ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ

ሰኔ 30/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ፒኤችዲ) የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ያለበትን ደረጃ ጎበኙ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ “የስታዲየሙን ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት አጠናቀን በአኅጉር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንዲሆን ለማድረግ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊ በጀት መድቧል” ብለዋል።

በአንድ በኩል የክልላችን ሰላምና ጸጥታ በማረጋገጥ፤ በሌላ በኩል የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቀን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ልማታችን ለማፋጠን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጠን እንሰራለን ሲሉም ገልጸዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW