ታኅሣሥ 13/2015 (ዋልታ) ፖርቹጋላዊው ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲ አረቢያውን ክለብ አል-ናስርን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል፡፡
የ37 ዓመቱ ተጫዋች በቅርቡ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በስምምነት መለያየቱን ተከትሎ ቀጣይ ማረፊያው የት ይሆናል የሚለው ጉዳይ እያነጋገረ ይገኛል፡፡
የስፔኑ ተነባቢ ጋዜጣን ማርካን ጨምሮ የተለየያ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን የፖርቹጋላዊው ኮከብ ቀጣይ ማረፊያ የሳዑዲ አረቢያው ከለብ አል ናስር ለመሆን ስለመቃረቡ አስነብበዋል፡፡
ክርስቲያኑ ሮናልዶ የዝውውር ሂደት ለማጠናቀቅ የተቃበ ሲሆን በአዲሱ ክለብ አል ናስር የ7 ዓመታት ውል ለመፈረም መስማማቱ ተነግሯል፡፡
የ5 ጊዜ የባላንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሳዑዲው ክለብ ለሁለት ዓመታት ተኩል በተጫዋችንት ካገለገለ በኋላ በቀሪዎቹ ዓመታት በክለቡ አምባሳደርነት ያገለግላል ተብሏል፡፡
የክርስቲያኖ ሮናልዶ ዝውውር በቀጣይ ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን በሳዑዲው ክለብ በዓመት 175 ሚሊየን ዩሮ ያገኛል ነው የተባለው፡፡
በመሠረት ተስፋዬ