የኬኒያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አገራዊ ችግኝ የመትከል ዘመቻን አስጀመሩ

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ

ታኅሣሥ 13/2015 (ዋልታ) የኬኒያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በደቡብ ኬኒያ በመገኘት አገራዊ ችግኝ የመትከል ዘመቻን አስጀመሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ዘመቻውን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጫና ለመቋቋም የአካባቢ ጥበቃ ስራን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል፡፡

ተከታታይ የችግኝ ተከላ ስራዎችን በማከናወን አስከ ፈረንጆቹ 2032 አገሪቱን 30 በመቶ በደን ለመሸፈን እቀድ መያዙን ተናግረዋል፡፡

ምድራችን ለሰው ልጆች ምቹ የምናደርግበት ጊዜው አሁን ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ሀገራችንን አረንጓዴ በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ተጽዕኖ እንከላከል ማለታቸውን የኬኒያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡