13ኛው ከተማ ዐቀፍ የባሕል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

                         13ኛው ከተማ ዐቀፍ የባሕል ፌስቲቫል

ጥር 15/2014 (ዋልታ) 13ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዐቀፍ ባሕል ፌስቲቫል “የባህል እሴታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መልዕክት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የከተማ አስተዳደሩ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ኪነ ጥበብ ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በፌስቲቫሉ ተገኝተዋል።

የቢሮ ኃላፊዋ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) በፌስቲቫሉ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር ከጥር 15 እስከ 17/2014 ዓ.ም በሚቆየው ፌስቲቫል የሀገር ባህል ምርቶች እና በአገር በቀል እውቀት የተሠሩ ምርቶች ለግብይት እና ትእይንት ይቀርባሉ ብለዋል።

ሁሉም አካል በንቃት እና በእውቀት ከባህላቱ ትሩፋት ለመጠቀም የበኩሉን አስተዋጽኦ መወጣት አለበት ያሉት ኃላፊዋ ጠላቶቻችን በሚሠጡንን አጀንዳ ሳንወሰድ ሰላም እና እድገታችንን በሚያፋጥኑ ነገሮች ላይ ትኩረት አድርገን መሥራት ይገባናልም ብለዋል።

“የባህል እሴታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መልዕክት የሚካሄደው ፌስቲቫል ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ኢፕድ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://www.facebook.com/waltainfo
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!