142 የሽብር ቡድኑ አባላት መደምሰስ

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው ወራሪው የሕወሓት አሸባሪ ቡድን በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አፀፋዊ እርምጃ ተወሰደበት፡፡

በዚህም 142 የሽብር ቡድኑ ታጣቂ ኃይል ሲደመሰስ 4 ስናይፕር ፣ 6 የሞርታር ቅንቡላ ፣ 1 ብሬን ፣ 18 የእጅ ቦምብ ፣ 15 ክላሽ ፣ 7 ሺሕ የብሬን ጥይት ፣ 5 ሺሕ የክላሽ ጥይት ፣ 1 የመገናኛ ሬዲዬ (1187 አይኮም) ፣ 1 የዋይፋይ ሪሲቨር ፣ 6 የብሬን ሻንጣና 10 የነፍስ ወከፍ ወታደራዊ የወገብ ሻንጣ ከጠላት ተማርኳል።

ከግንባሩ አመራሮች መካከል የክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል እንደተናገሩት ጠላት አሁን ላይ በሰራዊቱ እየደረሰበት ባለው ኪሳራና ባጋጠመው ሽንፈት የተስፋ መቁረጥ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው።

ይሁን እንጅ ከገባበት መግደያ ወረዳ መውጣት እንደማይቻለው ጠቅሰው፥ ወራሪውን ኃይል በገባበት በማስቀረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሕዝቡ የድል ዜና እናሰማለን ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡