1443ኛው የኢድ አል አደሃ በዓል በተለያዩ ከተሞች በድምቀት እየተከበረ ነው

ኢድ አል አደሃ በዓል

ሐምሌ 2/2014 (ዋልታ) የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ከተሞች በድምቀት እየተከበረ ነው።

1443ኛው የኢድ አላድሃ (አረፋ) በዓል በሐረሪ ክልል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

የክልሉን ርዕሰ መስተደድር ኦርዲን በድሪን ጨምሮ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በክልሉ በሚገኙ መስጂዶች በዓሉን በሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እያከበሩ ይገኛሉ።

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፣ የሀገርን ሰላም እና አንድነት በሚያረጋግጡ ሁኔታ እያከበሩት እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በአርባምንጭ ከተማ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በታላቁ ጃሚ መስጅድ አደባባይ እያከበረ ነው።

በዓሉ ሕዝበ ሙስሊሙ ለአቅመ ደካሞች በመስጠት በፍቅርና በአንድነት የሚያከብሩበት መሆኑም ተገልጿል፡፡

በሙስሊሙ ዘንድ ከበዓላት መካከል ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውና የእርድ በዓል በመባል የሚታወቀው የዒድ አል-አድሐ (ዐረፋ) በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማም በድምቀት እየተከበረ እንደሚገኝ የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW