1443ኛው የዒድ አል-አድሃ አረፋ በዓል በጅግጅጋ ከተማ ተከበረ

ሐምሌ 2/2014 (ዋልታ) 1443ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል-አድሃ አረፋ በዓል በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ተከብሯል።

በዓሉ በጅግጅጋ ስታዲየም ሲከበር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና የአምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የአረፋ በዓል በክልሉ 11 ዞኖች እና 93 ወረዳዎችም በድምቀት መከበሩን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW