1443ኛው የአረፋ በዓል እየተከበረ ነው

1443ኛው የአረፋ በዓል

ሐምሌ 2/2014 (ዋልታ) 1443ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በአዲስ አበባ እየተከበረ ባለው በዓል የሶላት ሥነ ሥርዓት ላይ የሚታደሙ የእምነቱ ተከታዮች ትንሿ ስታዲየም እየገቡ ነው።

በአሁኑ ወቅት በስታዲየሙ ምስጋና የሚቀርብበት ተክቢራ እየተደረገ ሲሆን ተክቢራው እንደተጠናቀቀም የሶላት ሥነ ሥርዓት የሚካሄድ ይሆናል።

አማኞች ከሶላት በኋላ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ እርድ በማካሄድ እና ለሌላቸው በማካፈል በዓሉን ያሳልፋሉ ተብሏል።

የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በዛሬው ዕለት በመላው ዓለም ለ1443ኛ ጊዜ በእስልምና ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ይውላል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW