152 ሺሕ ተማሪዎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን እንደሚቀላቀሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

መጋቢት 6/2014 (ዋልታ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152 ሺሕ የሚሆኑት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን እንደሚቀላቀሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ይህም በአማካይ በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ፈተናውን 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ካመጡት ውስጥ 53 በመቶ ያህል መሆኑ ተነግሯል።

በመንግሥት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63 ሺሕ 833 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135 ሺሕ 209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር እንደሚችሉም ተነግሯል።