ሐምሌ 28/2013 (ዋልታ) – 157 ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ የጭነት መኪናዎች መቀሌ መድረሳቸውን የአስቸኮይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡
የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አስፈላጊ መገልገያዎችን የያዙት የጭነት መኪናዎች፣ ከዓለም የምግብ ድርጅት፣ እንደ ዩኒሴፍና ዩ.ኤን .ኤፍ.ፒ.ኤ ካሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች፣ እንዲሁም ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍን ለማቅረብ ከሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተገኘ ድጋፍን አካትተዋል።