ግንቦት 5/2014 (ዋልታ) የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ 165 ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል ደርሰው 3 ሺሕ ቶን ምግብ ማከፋፈሉን አስታወቀ፡፡
የምግብ አቅርቦቱ 120 ሺሕ ዜጎችን ተደራሽ ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡
3 ሺሕ 400 ቶን የምግብ እርዳታ ደግሞ ወደ ማከፋፈያ ጣቢያዎች መላካቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም አሁን ላይ እርዳታ የጫኑ 94 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እያቀኑ ነው ተብሏል፡፡
የምግብ እርዳታ ስርጭቱ በአፋር እና በአማራ ክልልም በሂደት ላይ መሆኑን የዓለም የምግብ ፕሮግራም በማኅበራዊ የትስስር ገፁ ገልጿል።