16ኛው የኢትዮ ጅቡቲ የሚኒስትሮች ጉባኤ ፍሬያማ እንደነበር ተገለጸ

16ኛው የኢትዮ ጅቡቲ የሚኒስትሮች ጉባኤ

ጥቅምት 17/2015 (ዋልታ) 16ኛው የኢትዮ ጅቡቲ የሚኒስትሮች ጉባኤ ፍሬያማ እንደነበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው 16ኛው የኢትዮ ጅቡቲ የሚኒስትሮች ጉባኤ የተጠናቀቀ ሲሆን በማጠቃለያ መድረክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ አሊ የሱፍ ተገኝተዋል።

ጉባኤው ሁለቱን ሀገራት በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ እና ትራንስፖርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

በማጠቃለያ መርኃ ግብር ጅቡቱ ከኢትዮጵያ የኤለክትሪክ ኃይል ለመግዛት የሚያስችላት ስምምነትም ተፈራርመዋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሦስት ዓመታት ያህል ተቋርጦ የቆየው የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ጉባኤ ዛሬን ጨምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በመስከረም ቸርነት

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW