17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በሀዋሳ ይከበራል

ጥቅምት 4/2015 (ዋልታ) 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ”ሕብረብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሠላም” በሚል መሪ ቃል በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስተናጋጅነት በሀዋሳ ከተማ ይከበራል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዓሉን አስመልከቶ የበዓሉን ዓላማና መሪ ቃሉን መነሻ በማድረግ በበዓሉ ዕቅድ ላይ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከምሁራን፣ ከፌዴራልና ከክልሎች ከተውጣጡ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር እየተወያየ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡