ጥር 17/2014 (ዋልታ) “የአርብቶ አደሩ ልማት ለአገር ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል 18ኛው የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ቀን በአዳማ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ አርብቶ አደሮች እና የአርብቶ አደር ተወካዮች ተገኝተዋል።
በአገሪቱ ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም የአርብቶ አደሩን ህይወት ለመቀየር እየተሰራ ያለውን ሥራ በሁሉም ክልሎች በማስቀጠል ከውጭ የሚገባ የምግብ ፍጆታን በማስቀረት የውጭ ጫናን መቀነስ እንደሚገባ በበዓሉ ተገልጿል።
ታሪኳ መንግስተአብ (ከአዳማ)