19ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ በመዲናዋ እየተካሄደ ነው

ግንቦት 3/2014 (ዋልታ) የዲጂታል ይዘትና አገልግሎት ላይ ያተኮረው 19ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ የባህልና የቋንቋ ብዝሃነት ያላቸው አገሮች የዲጂታል ይዘትና አገልግሎትን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ የዲጂታል አካታችነትን ማረጋገጥ ይገባቸዋል።
ኢትዮጵያ በዲጂታል 2025 ስትራቲጂዋ ላይ አካባቢያዊ የዲጂታል ይዘት እና አገልግሎትን በማካተት እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸው፤ የአገር ውስጥ የይዘት አቅራቢዎች፣ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች እና የዓለም ዐቀፍ የዘርፉ ተዋናዮች የዲጂታል ይዘቶችን ዘላቂነት በማረጋገጥ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽን ባለስጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ በበኩላቸው የኢትዮጵያን የዲጂታል ጉዞ ከግብ ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛ ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት ይፋ መሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም አብራርተዋል።
በኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ በሚካሄደው 19ኛው የዲጂታል አፍሪካ ጉባኤ ላይ ከ30 በላይ አገሮች የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪዎች እየተሳተፉ ነው፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!