መስከረም 15/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለ7ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል፡፡
በዚህም በተለያዩ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 1 ሺሕ 331 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው፡፡
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከማል ኢብራሂም ተመራቂ ተማሪዎች በቀጣይ በሚሰማሩበት የሙያ መስክ ሀገርን ተቀዳሚ አድርገው ለተጀመረው የእድገት እና የልማት ጎዳና የበኩላቸውን አበርክቶ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል::
ተማሪዎችም ምንም እንኳን ሀገር በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ በማለፏ መጀመሪያ በተያዘው የትምህርት ዘመን ለምረቃ ሳይበቁ ቢቆዩም፤ የዛሬዋን ቀን በትዕግስት መጠበቃቸው ምስጋና ሊቸረው ይገባል ብለዋል::
እንዲሁም ተመራቂ ተማሪዎች ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጠራ ሊያመሩ እንደሚገባም ተገልጿል::
በሄብሮን ዋልታው