ሰኔ 20/2014 (ዋልታ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺሕ 85 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 17 ሴቶች፣ 19 ህጻናት እና 1 ሺሕ 49 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ 43 ሺሕ 175 ኢትዮጵያዊያንን መመለስ ተችሏል፡፡