ጥቅምት 5/2014 (ዋልታ) 39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች 2ኛ ቀን ስብሰባው በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡
በዛሬው የቀን ውሎ በተለያዩ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች የሚመክር ሲሆን፣ በተለይም አህጉሪቱ በአጀንዳ 2063 ለማሳካት ያስቀመጠቻቸውን ግቦች ትግበራ የተመለከተ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
እንዲሁም ለአፍሪካ ህብረት አስፈፃሚ ምክር ቤት ከቀረቡ እጩዎች መካከል አዲስ የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ይሰየማል ተብሏል።
በስብሰባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማትን ጨምሮ የህብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ስብሰባው የአገራት መሪዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማኀበረሰብ ተቋማትና በሕብረቱ ስር የሚገኙ ተቋማት የሚያደርጉት በሶስተኛው አጋማሽ ዓመት ለሚያደርጉት ጥምር ውይይት አጀንዳዎች የሚቀርቡበት እንደሆነም ተነግሯል።
በደረሰ አማረ