ግንቦት 30/2013 (ዋልታ) – የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌትን በማስመልከት የግንዛቤ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ዛሬ እንግሊዝ ለንደን ዛሬ ይጀመራል፡፡
ሲቪክ ድርጅቶች ለንደን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ዘመቻ ለሁለት ወራት የሚቆይ ነው።
የዘመቻው ዋና ዋና አላማዎችም ግድቡ በስኬት እንዲጠናቀቅ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ እና በግድቡ ላይ ለሚሰሩ ዜጎች የሞራል እና የስነልቦና ድጋፍ እውቅና መስጠት ነው ተብሏል።
በሌላ በኩል ዘመቻው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን እና ለአካባቢው ህዝብ ስላለው ጠቀሜታ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ፣ ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን አባላት እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወዳጆች ለማሳወቅ ያለመ መሆኑን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ይህ የግድቡ የድጋፍ ዘመቻ ባለፈው አመትም ተመሳሳይ መካሄዱ ይታወሳል።