2 ሺህ 257 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ


ሰኔ 21/2013 (ዋልታ) –
2 ሺህ 257 ዜጎች በትላንትናው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በተለያዩ አገራት የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህም ባለፉት ወራት ከስምንት አገራት 25 ሺህ 472 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተጠቁሟል፡፡