ጳጉሜ 1/2013 (ዋልታ) በጉጂ ዞን፣ ጎሮ ዶላ ወረዳ፣ ቢታታ ቀበሌ ሠላም ለማደፍረስ ተግባር ሊውሉ የነበሩ 2 ሺህ 858 የክላሽ እና ብሬን ጥይቶች ተይዘዋል፡፡
ለዕኩይ ዓላማ ሊውሉ የነበሩት ተተኳሽ ጥይቶች፣ ታርጋ ቁጥሩ 35819A.A በሆነ የአይሱዙ መኪና ተጭነው መኪናው ወደ ኔጌሌ ሊያመራ ሲል በፀጥታ አካላት መያዛቸውን የጉጂ ዞን አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወልዴ ዱጎ አስታውቀዋል፡፡
ከተተኳሽ ጥይቶቹ በተጨማሪም 32 የጦር ሜዳ ልብሶች መያዛቸውንም የኦቢኤን ዘገባ አመላክቷል፡፡