2 ሺህ 573 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

ሐምሌ 04/2013 (ዋልታ) – 2 ሺህ 573 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎች በየቀኑ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 118 ሴቶችንና 72  ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 573 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን የያዘው ኮሚቴ አቀባበል እንዳደረገላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡