ኅዳር 2/2014 (ዋልታ) ሆፕ ሉን ኢትዮጵያ የተሰኘውና በባሕር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ የልብስ ስፌት ላይ የተሰማራው ኩባንያ 200 ሺሕ ዶላር የሚያወጣ የመጀመሪያ ዙር ምርቱን ለወጪ ገበያ ላከ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ እንደሚጠቁመው የሴቶች አልባሳትን እያመረተ የሚገኘው ኩባንያው አሁን ላይ ለ1 ሺሕ ሰዎች የሥራ ዕድል ሲፈጥር በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ ለ9 ሺሕ ሰዎች ቀጥተኛ ሥራ መፍጠር እንደሚችል ታምኖበታል፡፡
በሌላ ዜና የንግድ ማበረታቻውን አግዋ ለፖለቲካ ፍጆታአውሎ ኢትዮጵያን ከተጠቃሚነት የሰረዘውን የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር እርምጃ ተፅዕኖ ለመቋቋም አማራጭ ገበያና ምርቶች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳንዶካን ደበበ ተናግረዋል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ