ሐምሌ 07/2013 (ዋልታ) – 2 ሺህ 42 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ መመለሳቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በተያዘው እቅድ መሰረት በርካታ ዜጎቻችን በየቀኑ እየተመለሱ ይገኛሉ።
በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት 229 ሴቶችንና 136 ህጻናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 2 ሺህ 42 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ገብተዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን ያቀፈው ኮሚቴ ተገቢው አቀባበል እዳደረጉላቸው ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።