ፕሮጀክቱ ባለፉት 13ዓመታት ከ5ሺ በላይ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን አስገንብቷል

የአርብቶ አደር  ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት ባለፉት 13 ዓመታት  በአራት  ክልሎች  ከ 5ሺ  በላይ  የሚሆኑ  የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን ማስገንባቱን የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት  ጉዳዮች  ሚንስቴር አስታወቀ ።

በሚኒስቴሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ሰኢድ ኡመር ለዋልታ እንደገለጹት በአገሪቱ  የአርብቶ አደር አካባቢ  ተመጣጣኝ ልማት ለማምጣት  ከ1996 ዓም ጀምሮ የአፋር ፣ ሶማሌ ፣ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች  በአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት አማካኝነት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚሠጡ ተቋማት ሲገነቡ ቆይተዋል ።

ፕሮጀክቱ  አብርቶ አደር በሚበዛባቸው ክልሎች ተግባራዊ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሰኢድ ባለፉት 13 ዓመታት በ112 ወረዳዎች   የትምህርት ፣  የመጠጥ ውሃ ፣ የመንገድ ፣ የአርብቶ አደር ማሠልጠኛና የሰውና የእንስሳት  የጤና ተቋማት  መገንባታቸውን ተናግረዋል ።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብቻ ፕሮጀክቱ 774 ያህል የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን ለማስገንባት   በዕቅድ  ይዞ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሰኢድ 653  የሚሆኑት በፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው ለአርብቶ አደሩ አገልግሎት መሥጠት ጀምረዋል ብለዋል ።

ፕሮጀክቱ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተግባራዊ ከማድረጉ በፊት የአካባቢውን አርብቶ አደሩን  ያወያያል ያሉት አቶ ሰኢድ ማህበረሰቡ  ቅድሚያ  ለሚሠጠውና ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው የማህበራዊና  ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ግንባታ እንደሚከናወን ገልጸዋል ።

በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ አንስቶ በሦስት ምዕራፎች 1ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚሆኑ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረጉን  የገለጹት ሰኢድ እስካሁን  ከ 400 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጓል ።

የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ፕሮጀክት ከፊሉን  ወጪ የሚሸፈነው በኢትዮጵያ  መንግሥት ሲሆን  የዓለም አቀፉ ልማት ማህበር( አይዲኤ) እና  ዓለም አቀፉ  የምግብና የእርሻ ልማት ( ኢፋድ) በተገኘ ድጋፍ እየተካሄደ ይገኛል ።   

የአርብቶ አደር  ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት ባለፉት 13 ዓመታት  በአራት  ክልሎች  ከ 5ሺ  በላይ  የሚሆኑ  የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን ማስገንባቱን የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት  ጉዳዮች  ሚንስቴር አስታወቀ ።

በሚኒስቴሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ሰኢድ ኡመር ለዋልታ እንደገለጹት በአገሪቱ  የአርብቶ አደር አካባቢ  ተመጣጣኝ ልማት ለማምጣት  ከ1996 ዓም ጀምሮ የአፋር ፣ ሶማሌ ፣ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች  በአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት አማካኝነት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚሠጡ ተቋማት ሲገነቡ ቆይተዋል ።

ፕሮጀክቱ  አብርቶ አደር በሚበዛባቸው ክልሎች ተግባራዊ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሰኢድ ባለፉት 13 ዓመታት በ55 ወረዳዎች   የትምህርት ፣  የመጠጥ ውሃ ፣ የመንገድ ፣ የአርብቶ አደር ማሠልጠኛና የሰውና የእንስሳት  የጤና ተቋማት  መገንባታቸውን ተናግረዋል ።