በፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስትሮች ሲመራ የነበረው የኢትዮ-ጅቡቱ የጋራ ጉባዔ በመሪዎች ደረጃ እንዲሆን መወሰኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ውሳኔው የአገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚረዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ቀባይ አቶ ተወልድ ሙሉጌታ ለዋልታ አስታወዋል፡፡
የሁለቱ አገራት ጠንካራ ግንኙነት በምስራቅ አፍሪካ እንደ ማሳያ እንደሚጠቀስ አስገንዝበዋል፡፡
መሪዎቹ በጋራ ጉባዔው ላይ በአካል ተገናኝተው በፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከመነጋገር ባለፈ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በሚረዱ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች ዙሪያ ለመወያየት ይረዳቸዋል ብለዋል-አቶ ሙሉጌታ፡፡
የመሰረተ ልማት መስፋፋት የሁለቱን አገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ ቅንጅትን ለማጠናከር እንደሚረዳ አቶ ተወልድ ገልጸዋል፡፡
‹‹ኢትዮጵያ የሕዝብ ለህዝብ ግንኙነቱና ፖለቲካዊ ትብብሩ እንዲጠናከር ትፈልጋለች›› ብለዋል
በአሁን ወቅት ሥራ የጀመረው የጅቡቲ- ሜኢሶ- ሰበታ ባቡር ፕሮጀክት እና ከጅቡቲ ወደብ ታጅሮህ ወደ መቀሌ የሚዘረጋው የባቡር ፕሮጀክት የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያጋግረው ነው ያስታወቁት ፡፡
ኢትዮጵያ የጅቡቲ ወደብን በመጠቀም የንግድ ልውውጦችን እንደምታከናውን ይታወቃል ሲሉ ጠቅሰዋል ፡፡
ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይልና የመጠጥ ውሃን ከኢትዮጵያ የምታገኝ መሆኗንም አስታውሰዋል ፡፡
ትርጉም በዳንኤል ንጉሤ