የአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር መስመርን ወደ ስራ ለማስገባት ባለፈው ህዳር ወር 2009 ዓ.ም በኢትዮጵያና ጅቡቲ ጥምረት የተቋቋመው ድንበር ተሸጋሪ ሃላፊነት ያለው የጋራ ኩባንያ በቀጣይ ሳምንት ስራውን ይጀምራል፡፡
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታቸው በትሩ ዛሬ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ኩባንያው በኢትዮጵያ ህግ የሚተዳደር ይሆናል፡፡
በጥቂት ቀናት ውስጥ ህጋዊ አደረጃጀቱን አጠናቆ ወደ ስራ ይገባል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
የኩባንያውን ስራ መጀመር ተከትሎ የባቡር መስመሩ በመጋቢት ወር 2009 ዓ.ም የሙከራ አገልግሎት እንደሚጀምር ገልጸዋል፡፡
758 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውን የአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር መስመር መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ.ም በይፋ መመረቁ ይታወሳል፡፡