የቱርኩ ኢስታንቡል ከመርበርጋዝ ዩኒቨርስቲ ለፕሬዝደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በኢኮኖሚክስ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ፡፡
ፕሬዝደንቱ የኢትዮ-ቱርክን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በማሳደግ ረገድ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ከዩኒቨርስቲው የላቀ ክብር ተቀብለዋል፡፡
በኩልም የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሰሞኑን በቱርክ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ባሉበት ወቅት የአንካራ ዩኒቨርስቲ የወዳጅነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አበርክቶላቸዋል።
ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እንደአውሮፓ አቆጣጠር ከ2006 እስከ 2013 ለሰባት ዓመታት በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል።
በቱርክ አምባሳደርነት ቆይታቸውም በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረው ግንኙነት ከፍ ወደአለ ደረጃ እንዲሸጋገር ብርቱ ጥረት አድርገዋል-(ኢዜአ) ፡፡