ባንኩ የውጭ ምንዛሬ ላስገኙ ባለሃብቶችና ተቋሞች ሽልማት ሰጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወጪ ንግድ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የተለያዩ ባለሃብቶችና ተቋሞች የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ ፡፡

በሽራተን አዲስ ትናንት በተዘጋጀው የደንበኞች ቀን በዓል ላይ ከ1 ሚሊየን ዶላር እስከ 300 ሚሊየን ዶላር በላይ ላስገኙ ባለሃብቶችና የተለያዩ ተቋሞች የሰርተፊኬት፣የነሐስ፣የብርና የወርቅ ሽልማት ከባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በረከት ስመዖን፣ ከንግድ ሚኒስትሩ ዶክተር በቀለ ጉላዶ ና ከባንኩ ፕረዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ እጅ ተቀብለዋል ፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ በዚሁ ጊዜ ባሰሙት ንግግር ባላሃብቶችንና ተቋማትን መሸለም በተለይም በወጪ ንግድን በማሳደግ በአገሪቱ ዕድገት ላይ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ሚናው የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል ፡፡

ሽልማቱን ያገኙትም በወጪ ንግድ ፣በገንዘብ ዝውውርና በአገልግሎት ዘርፍ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ 127 ባለሃብቶችና የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት መሆኑን በስነ-ስርዓቱ ላይ ተመልክቷል ፡፡