በአውሮፓ ግዙፍ የሆቴሎች ኩባንያ የሆነው አከር ሆቴሎች በአዲስ አበባ ሶስት ሆቴሎችን ለመገንባት ስምምነት መፈጸሙን አስታወቀ
በቀጣይ አራት ዓመታት ሶስት ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችን በመገንባት በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ እንደሚቀላቀል ታውቋል።
ከኩባንያው በተገኘው መረጃ መሰረት ሆቴሎቹ 520 መኝታ ክፍሎች እንደሚኖሩት ታውቋል፡፡
በአውሮፓ የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ መዳከም ቢያሳይም እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ላይ መስራት አዋጪ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የሸራተን፣ ሒልተን፣ ራዲሰን፣ ማሪዮትና ጎልደን ቱሌፕ በኢትዮጵያ ቅርንቻፎቻቸውን ከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ ዓለምአቀፍ ሆቴሎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የአከር ሆቴሎች ኩባንያ በ40 ዓመት የአፍሪካ ቆይታው በ21 የአፍሪካ አገሮች 94 ሆቴሎችን ከፍቶ ለ10 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር እንደቻለም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡