በትግራይ ከ2ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ባለስልጣኑ አስታወቀ

በትግራይ ክልል ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ ፡፡

በገቢዎች ባለስልጣን የገቢ ዕቅድ ዝግጅት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሸዊት ሓጎስ ለዋልታ እንደገለጹት ፤በተያዘው በጀት ዓመት ከገቢ ግብር ፣ከሌሎች ገቢዎች፣ ከቀጥታ ታክስና ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶች ከ3 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል ፡፡

የባለስልጣኑ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ በመንፈቅ በጀት ዓመት ብቻ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቀዋል፡፡

ይህም ዓምና በተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው 1 ነጥብ 93 ቢሊየን ብር ጋ ሲነጻር ዘንድሮ የተወሰነ ብልጫ ያሳያል ነው ያሉት ፡፡

የዚሁ ምክንያትም ባለስልጣኑ ለንግዱ ማህብረሰብ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ በስፋት በመስጠቱና እና ደረሰይ በመቀበል ረገድ ያለው ባህል እንዲያጎለብት ከፍተኛ ጥረት በመደረጉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡