የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፈቃድ መሥጠቱን አስታወቀ ።
የክልሉ የኢንቨስትመንት ቢሮ የኢንቨስትመንት ማስፋፋያ ኃላፊ አቶ ክብረ ወሰን መኩሪያ ለዋልታ እንደገለጹት የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከተሠጣቸው ከ72 ፕሮጀክቶች ውስጥ 44 የሚሆኑት በግብርና የተሠማሩ እንዲሁም የቀሩት በማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽንና በአገልግሎት ዘርፍ የሚሠማሩ ናቸው ።
የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግሥት በግብርና ዘርፍ ለሚሠማሩት ባለሃብቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ መሬት ለመሥጠት እየሠራ ይገኛል ብለዋል አቶ ክብረወሰን ።
በቤኒሻንጉል ክልል በኢንቨስትመንት ለሚሠማሩ ባለሃብቶች በሚሠጠው ድጋፍ ምክንያት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚሠማሩ ባላሃብቶች ቁጥር ከባለፈው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ዕድገት አሳይቷል ።