ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በሀገር ውስጥ ከሚደረገው ርብርብ ያልተናነሰ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮያውን ድጋፍ ማድረግ መቀጠላቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
የሚኒስትሩ ቃለ አቀባይ ቃል አቀባዩ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ለዋልታ እንደገለጹት፤እስካሁን በገንዘብ ብቻ ከ36 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ይሁንናመንግስት በገንዘብ ማሰባሰብ ስራው ላይ ችግር እዳጋጠመው አሳውቋል፡፡
በአለም ዙሪያ ተሰራጭተው የሚገኙኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮያውን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄድ በአሁኑ ሰአት ከ 3 ሚሊየን በላይ ደርሷል ብለዋል ፡፡
ይህን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የማህበረሰብ ክፍል ታዲያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በሀገሪቱ እየተካሄዱ ባሉታላላቅ ፕሮጀክቶች ላይ ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጀምሮ የበኩላቸውን ሚና በመወጣት አሻራቸውን እንዲያሳርፉ መንግስት እየሰራሁ ነው ይላሉ፡፡
ይህንኑ ተከትሎም በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮያውን ባለፉት ጥቂት አመታት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብቻ ከ 36 ሚሊየን ዶላር የላቀ ገንዘብ ደጋፍ ማድረጋቸውን አመልክተዋል ፡፡
ከዉጪ ጉዳይሚኒስቴር ጋር በመተባበር ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትጵያዉያኑ በሀገራቸዉ አጠቃላይ ግንባታ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ እየሰራ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር አባላቱ ግድቡን ከመጎብኘት ጀምሮ እስከ ገንዘብ ድጋፍ እንዲሳተፉ የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉኑ ለግድቡ በሚያደረጉት ድጋፍ እያጋጠሙ ያሉ መሰናክሎች አልጠፉም ብለዋል፡፡
በተለይም በአሜሪካ ከሀገሪቱ የቦንድ ሽያጭ አሰራር ጋር በተገናኘ በተፈጠረዉ ችግር የገንዘብ ድጋፉ መቋረጡን የግድቡን ስድተኛ አመት የምስረታ በአል አስመልክቶ በተሰጠዉ መግለጫ ላይ ገልጸዋል፡፡
የግድቡን ስድስተኛ አመት የምስረታ በአል በማስመልከት በአለም ዙሪያ በኢትዮጵያ ሚስዮኖችና ኢምባሲዎች ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን በማሰናዳት ድጋፉን የበለጠ ለማጠናከር አቅደዉ በመስራት ላይ መሆናቸዉም ታዉቋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስከ የካቲት ወር 2009 ዓ.ምድረስ 56 በመቶ መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡
አርታኢ -በሪሁ ሽፈራው