በአዲስ አበባ 60 በመቶ መንገዶች የኤሌክትሪክ መሥመር የተዘረጋላቸው ነው

በአዲስ አበባ ከተማ 60 በመቶ የሚሆኑት የአስፓልት መንገዶች ለመንገድ  መብራት አገልግሎት ሊውል የሚችል  የኤሌክትሪክ  መሥመር  የተዘረጋላቸው መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች  ባለሥልጣን አስታወቀ ።

የባለሥልጣኑ ዋና ኃላፊ ልዩ ረዳት  አቶ ሲሳይ  ወርቅነህ ለዋልታ እንደገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ  5ሺ 900  ኪሎሜትር የሚሆን  የአስፋልት መንገድ ሽፋን ቢኖራትም 60 በመቶ በሚሆነው መንገድ ብቻ ነው  ለመብራት አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሪክ መሥመር የተዘረጋው ።

በአዲስ አበባ ከተማ መብራት  ያላቸው መንገዶች በቁጥር አነስተኛ  በመሆኑ   መብራት ያላቸው መንገዶችን ቁጥር  ለማሳደግ  ተጨማሪ ሥራዎችን ሊሠሩ እንደሚገባ ለዋሚኮ አስተያየታቸውን የሠጡ የከተዋማ ነዋሪዎች ተናግረዋል ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን መካከል ተቀናጅቶ የመሥራት ክፍተት በመኖሩ ምክንያት ችግሮች  መባባሳቸው ተገልጿል ። 

( አርታዒ- ሰለሞን ተስፋዬ  )