ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን ኢኮኖሚ ካስመዘገቡ አምስት ሃገራት ሁለተኛ መሆኗን የዓለም ፋይናንስ ተቋም አስታወቀ ፡፡
ተቋሙ የዓለም ባንክ ሪፖርትን ጠቅሶ የ200 የዓለም ሃገራትን ኢኮኖሚያዊ እድገት በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን ኢትዮጵያ ከቡታን አገር ቀጥሎ በሆለተኛ ደረጃ ነው ያስቀመጣት ፡፡
ኢትዮጵያ ከድሃ ሃገራት ውስጥ በመሆን በርካታ የልማት ሜጋ ፕሮጀክቶች በመተግበር በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ የምትገኝ በመሆኗ ነው እድገቱ ልታገኝ የቻለችው ብሏል ፡፡
በዚሁም ኢትዮጵያ በ8 ነጥብ 7 በመቶ ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስመዝገቧን የጠቀሰው የዓም ፋይናስ በሪፖርቱ ፤
ኢትዮጵያ እንደአውሮፓ አቆጣጠር ከ2004 እስከ 2014 ባሉት ዓመታትም በህዝብ መሰረተ ልማትና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ኢትዮጵያ ፈጣን እምርታዊ ለውጥ መሳየቷን ገልጿል ፡፡
በተለይም የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሃገሪቱን ወደ ከፍተኛ እድገት ሊያስገቧት የሚችሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ መሆኗን ነው ያስታወቀው
እንደአውሮፓ አቆጣጠር ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በፍጥነት እያደገ መሆኑን አስረድቷል፡፡
ሃገሪቱ አሁን በያዘችው ፍጥነት በማደግም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ እንደምትሰለፍ ነው ያመለከተው፡፡
በአንደኛ ደረጃ የተቀመጠችውና በህንድና በቻይና መካከል የምትገኘው ቡታን ለመሰረተ ልማት የማትመች ተራራማ ብትሆንም በእርሻና በተፈጥሮ ሃብት በሰራችው ውጤታማ ስራ ኢኮኖሚዋ 11 ነጥብ 1 በመቶ ማደፈጉን ነው ያብራራው ፡ ፡
ከኢትዮጵያ ቀጥሎም ጋናና ኮቲዲቯር በእኩል 8 ነጥብ 1 ሶስተኛ ፣ህንድ በ7 ነጥብ 7 ኢኮኖሚያዊ እድገት አምስተኛ ደረጃ ላይ መሆናቸውን የዓለም ፋይንስ ተቋም ገልጿል ፡፡
ምንጭ፡– www.worldfinance.com