የሞጆ ደረቅ ወደብን ለወጪ ንግድ እቃዎች አገልግሎት እንዲውል ለማደረግ የመሠረተ ልማት ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ ።
የድርጅቱ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ተፈራ እንደገለጹት የሞጆ ደረቅ ወደብ በአሁኑ ወቅት ለገቢ እቃዎች ብቻ አገልግሎት እየሠጠ መሆኑን ተናግረዋል ።
ለወደፊቱ ደረቅ ወደቡ የወጪ እቃዎች አገልግሎት እንዲሠጥ ለማድረግ የአምስት ዓመት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ተጠባባቂ ሥራ አስፈጻሚው አያይዘው ገልጸዋል ።
ከዓለም ባንክ በተገኘው 150 ሚሊዮን ዶላር ብድር የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ለወጪ እቃዎች አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን እንደሚሟሉ ይጠበቃል።