ድርጅቱ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን የማቅረብ ቁልፍ ሚናው እየጫወተ ነው

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓት ልማት ድርጅት  የአገር ውስጥ ጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ኢንዱስትሪዎች የግብዓት እጥረት እንዳይገጥማቸው ተገቢውን ሚና እየተጫወተ መሆኑን አስታወቀ ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስፋወሰን መሓሪ  ለዋልታ እንደገለጹት፤ በአገር ውስጥ የሚገኙ  የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ኢንዱስትሪዎች  የሚያስፈልጋቸውን የጥጥና የጥሬ ቆዳ ግብዓቶች በማቅረብ ረገድ  የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓት ልማት ድርጅት አበረታች ሚና እየተጫወተ ይገኛል ።

ድርጅቱ ግብዓቶችን  በጥራትና በብዛት  ለማቅረብ እንዲያስችለው  በጋምቤላና በደቡብ ኦሞ ተጨማሪ መጋዘኖችን ለመክፈት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተገልጿል ።

የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ጥራት ያለውና  የግብዓት አቅርቦት ችግር  ፈተና  ሆኖባቸው የቆየ  ቢሆንም  ድርጅቱ መቋቋሙ   ችግሮችን  እየተቃለሉ እንዲመጡ  የላቀ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ተመልክቷል ።

መንግሥት  በአምራች ኢንዱስትሪው ለሚሠማሩ  የአገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች  የቀረጥና ሌሎች የማበረታቻ ሥርዓት  ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የኢንዱትሪ ሚንስቴር ያወጣው  መረጃ ያመልክታል ።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓት ልማት ድርጅት በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር  328/2006  የኢንዱስትሪ ግብዓት ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋቋመ ሲሆን በ 2007 ዓም መጨረሻ ሥራ  ግብዓቶችን ማቅረብ ጀምሯል ።