የትግራይ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለ20 ቀናት ሲያከናውነው የቆየው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የዘመቻ ሥራዎችን ማጠናቀቁን አስታወቀ ።
በክልሉ የግብርናና የገጠር ልማት ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ልማት አስተባባሪ አቶ አረፈ ኪሮስ ለዋሚኮ እንደገለጹት በክልሉ በ 34 ወረዳዎች በሚገኝ ከ103 ሺ ሄክታር በላይ መሬት በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራዎች ተሸፍኗል ።
በዘመቻው ሥራው ከጥር ወር መጨረሻ አንስቶ የተከናወነ ሲሆን 1ነጥብ4 ሚሊዮን ህዝብ በየዕለቱ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ አስተዋጽኦ አበርክቷል ።
የክልሉ የግብርናና የገጠር ልማት ቢሮው በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የዘመቻ ሥራ 100 ሺ ሄክታር መሬትን ለመሸፈን ታቅዶ የክልሉ ህዝብና አመራሩ ባደረገው ርብርብ 103 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የዘመቻው ሥራ መከናወኑን አቶ አረፈ ገልጸዋል ።
እንደ አቶ አረፈ ገለጻ በዘንድሮ የበጀት ዓመት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የዘመቻ ሥራ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የውሃ ጉድጓዶችን በማበልጸግና ድርቅን ለመቋቋም በሚያችል መልኩ ተካሄዷል ።
የክልሉ ህዝብም በዘመቻ ሥራው ያደረገው ተሳትፎ ሊደነቅ እንደሚገባው አቶ አረፈ ጠቁመዋል ።