ለአምስት ቀናት የሚቆየው 3ኛው የምግብናመጠጥ አውደ ርዕይ በትናንትናው ዕለት ተከፈተ
የምግብና የመጠጥ ፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከኤስ ፒ ጀነራል ቢዝነስ ጋር በመሆን ነው 3ኛው የምግብና መጠጥ አውደ ርዕይ ተዘጋጅቶ በትናንትናው ዕለት የተከፈተው ።
አውደ ርዕዩ “ ጥራት ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን የአገር ውስጥ የምግብና የመጠጥ ምርቶች ላይ የተሠማሩ አካላትን በመደገፍ አገሪቱ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪን ለማስቀረት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል ።
የአገር ውስጥ አምራቾች ሆነው ከውጭ አገር የሚገቡ የምግብና መጠጥ ምርቶችን ለመተካት የሚሠሩ ድርጅቶችን በዋነኝነት በአውደ ርዕዩ እንዲሳተፉ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ እገዛ እንደሚኖረው ታምኖበታል ።
በተጨማሪም አውደ ርዕዩ የሀገር ውስጥ አምራች ተቋማት ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበትና እርስ በራሳቸዉ ግንኙነት የጋራ ህብረት የሚፈጥሩበትም ይሆናል ተብሏል፡፡
በ3ኛው የምግብና መጠጥ አውደ ርዕይ ከ70 በላይ የሚሆኑ አምራች ድርጅቶች እየተሳተፉ ይገኛል ፡፡