ኢትዮጵያ ባለፉት አሥር ዓመታት በጤናው ዘርፍ ዕድገት ማስመዝገቧን ቻይናዊው ዶክተር ው ሚንሽያን ገለጹ

ዶክተር ው ሚንሽያን  “በአፍሪካ የአሥር ዓመታት ቆይታዬ” የሚል ርዕስ  ባለው  ለንባብ  በበቃው መጽሓፋቸው እንደጠቀሱት  ኢትዮጵያ ባለፉት አሥርት ዓመታት በጤናው ዘርፍ  ግንባር ቀደም የሆነ ዕድገት አስመዝግባለች።   

በቱሉ ቦሎና በአዲስ አበባ ጥሩነሽ ዲባባ ቤጂንግ ሆስፒታል ለአራት ዓመት የህክምና አገልገሎት ሲሰጡ  የቆዩት ዶክተር ው ሚንሽያን በኢትዮጵያ የቻይና  የህክምና ቡድን አባል በመሆን  የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አብርክተዋል ፡፡

ዶክተር ዉ ሚንሽያን  እንደገለጹት ኢትዮጵያ የጤና ተቋማትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግና አገልግሎቱን በማስፋት ረገድ ባለፉት አሥር ዓመታት ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት የተሻለ ለውጥ አስመዝግባለች ብለዋል ።  

የጤና ተቋማትን ለሕዝቡ ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ የመስኩን ባለሙያዎች ቁጥር በማሳደግና አገልግሎቱን በማስፋትም የሚበረታታ ለውጥ እያመጣች እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ዶክተር ው በመጽሐፋቸው ቻይናዊያን የህክምና ባለሙያዎች እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1960ዎቹ ጀምሮ በአፍሪካ የሠጡትን አገልግሎትና ለአፍሪካ-ቻይና ትብብር መጎልበት ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ዳሰዋል፡፡( ኢዜአ)