ሚኒስቴሩ 3ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች መፍላታቸውን አስታወቀ

በያዝነው ክረምት 3ነጥብ5 ቢሊዮን ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ሚኒስቴሩ አስታወቀ

በመላ አገሪቱ ለሚካሄደው  የችግኝ  ተከላ  መርሃ ግብር  3ነጥብ5 ቢሊዮን ችግኞች መፍታላቸውን የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር  አስታወቀ ።

የሚኒስቴሩ የደን ልማትና እንክብካቤ ዳይሮክቶሪየት ዳይሬክተር ወይዘሮ አብረኸት ገብረህይወት ለዋልታ እንደገለጹት፤ በያዝነው ክረምት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ህብረተሰቡን  ባሳተፈ ሁኔታ ለሚካሄደው የችግኝ ተከላ ዘመቻ የሚውል  3ነጥብ5 ቢሊዮን ችግኞች ፈልተው ተዘጋጅተዋል  ።

እንደ ወይዘሮ አብረኸት ገለጻ ለተከላ ዝግጁ ከሆኑት ችግኞች መካከል የተወሰኑት በበልግ ወቅት ዝናብ  ባገኙ አካባቢዎች የተተከሉ መሆኑን ጠቅሰው ፤ክረምት ወቅት የሚተከሉ ።

ችግኞቹ  በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በሚገኝ ግማሽ  ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ የሚተከሉ   መሆኑን አመልክተዋል ።

በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው የዝናብ እጥረት ምክንያት የችግኝ የማፍላትና የመትከል ሥራውን አስቸጋሪ  ማድረጉን ወይዘሮ አብረኸት ጠቁመዋል ።

ህብረተሰቡ ችግኞችን ከተከለ በኋላ አስፈላጊው እንክብካቤ በማድረግ  እንዲጸድቁ ማድረግ ይገባዋል  ነው ያሉት ፡፡

ለዚሁም ህብረተሰቡ ችግኞችን በተገቢው መልሉ እንክብካቤ እንዲያደርግ  የግንዛቤ  የማስጨበጥ ሥራው  ተጠናክሮ መቀጠሉን በመጠቆም  ።

የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በ2008 ዓም ሁለተኛ   አጋማሽ  በአገሪቱ የችግኝ መጽደቅ ደረጃ  67 በመቶ  ተመዝግቧል ።

የአገሪቱ የደን ቆጠራ መረጃ እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በአሁኑ ወቅት  15ነጥብ5  በመቶ  መሆኑ መድረሱ ነው የጠቀሱት  ።