በአማራ ክልል በበቆሎ ማሳ ላይ የተከሰተውን ተምች ለመከላከል መቻሉ ተገለጸ

በአማራ ክልል 89 ሺህ ሄክታር በሚሸፍን የበቆሎ ማሳ ላይ የተከሰተውን ተምች መከላከል መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል፡፡

ተምቹ በክልሉ በቆሎ አብቃይ በሆኑ አምስት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 54 ወረዳዎች መስፋፋቱን በቢሮው የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ቁምላቸው ተናግረዋል፡፡

በተምች ከተወረረው 103 ሺህ ሄክታር መሬት እስካሁን 89 ሺህ ሄክታሩን በባህላዊ ዘዴና ኬሚካል በመርጨት መከላከል ተችሏል። ( ኢዜአ)