ምክር ቤቱ በ2011 በጀት ላይ ውይይት አካሄደ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በ2011 ረቂቅ በጀት ላይ ዝርዝር ወይይት አካዷል።

የምክር ቤት አባላት የቀጣይ ዓመት ረቂቅ በጀትን የተመለከቱ የተለያዩ ጥያቄዎች በማቅረብ  ጭምር ውይይት አድርገዋል ።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚንስትር ዶክተር አብረሃም ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች  ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መንግሥት በ 2011 የያዛቸውን እቅዶች ለመተግበር የገቢ አሰባሰብ ላይ ትኩረት ሠጥቶ እንደሚሠራ  ተናግረዋል ።

በ2011 ረቂቅ  በጀት ለክልሎች የሚደረግ ድጋፍ ከ 2010 በጀት ጋር ሲነጻጻር በ16 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉን ዶክተር አብርሃም አያይዘው ገልጸዋል ።

ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በሚያካሄደው ልዩ ስብሰባ የኢፌዴሪ  ጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር አብይ አህመድ  በተገኙበት በረቂቅ በጀት ላይ ውይይት አድርጎ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል ።   

የሚንስትሮች ምክር ቤት የ2011 ዓም በጀትን 346 ቢሊዮን 915 ሚሊዮን 415ሺህ 948  እንዲሆን  ለምክር ቤቱ ማቀረቡ ይታወሳል ።