የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ሂሳብ ቁጥር ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ይፋ ሆነ።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን  የአገር ልማት ለማገዝ ከእለት ፍጆታቸው አንድ ዶላር እየቀነሱ ለአገራቸው ልማት ቢለገሱ መንግስት በጥንቃቄ ይዞ ስራ ላይ እንደሚያውልም ገልጸው ነበር።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንደገለጸው  በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ወደ አገር ቤት የሚልኩበት የባንክ አካውንት በአትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከፍቷል።

በመሆኑም የዲያስፖራውን ተሳትፎ ለማቀናጀትና የልገሳውን ገንዘብ ለማሰባሰብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “Ethiopian diaspora trust fund” በሚል ስም የተከፈተ ሲሆን፤ የሂሳብ ቁጥሩም 1000255726725 ነው።

በመሆኑም ወደ ተከፈተው “Ethiopian diaspora trust fund” ሂሳብ ገንዘብ ገቢ ሲደረግ በቅርቡ በሚዘጋጀውና ለዳያስፖራው ይፋ በሚደረገው ድህረ ገጽ በመጠቀም፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የSWIFT አድራሻ CBETETAA እና ሌሎች  ከንግድ ባንኩ ጋር የሚሰሩ የውጭ አገር ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን በመጠቀም መሆን እንዳለበት ተመልክቷል።(ኢዜአ)