የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ዓለም አቀፍ ጉባዔ እያካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር አስራ ስድስተኛውን ዓለም አቀፍ ጉባዔ ማካሄድ ጀመሯል፡፡

ማህበሩ በአሁኑ ጉባዔው  በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በተለያዩ ክፍለ ኢኮኖሚዎች ላይ የተደረጉ ጥናቶችን ይመለከታል፡፡

በጉባዔው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚስትር ደመቀ መኮንን  መንግስት ማህበሩ  ለሚያከናውነው  የምጣኔ ሀብታዊ ጥናቶች እንቅስቃሴቀዎች ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ጉባኤው በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታ የማህበሩ አባላትና ተጋባዥ የኢኮኖሚ ምሁራን በሚያቀርቧቸው ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ ውይይት ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ገለልተኛ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ ማህበር ነው፡፡

ማህበሩ ከምጣኔ ሀብት ጋር በተያየዙ ጉዳዮች ጥናት በማድረግም ለፖሊሲ አውጭ አካላት ምክረ ሀሳብ ያቀርባል ፡፡