የደቡብ ክልል ምክር ቤት 37 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን በጀት አፀደቀ

የደቡብ ክልል መንግሥት በዛሬው ዕለት በምክር ቤት የቀረበለትን 37 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር   2011 ዓም በጀት አፅድቋል፡፡

በጀቱ ከፌዴራል መንግስት ድጎማ፣ ከክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ እና  ከሌሎች የገቢ ምንጮች በሚገኘው ገንዘብ ይሸፈናል ነው የተባለው፡፡

ይህ በጀት ለክልል ማዕከል መስሪያ ቤቶች መደበኛና የካፒታል ወጪ 3 ቢሊየን 919 ሚሊየን 551 ሺህ ብር፣ ለዞኖች፣ልዩ ወረዳዎች እና ለሓዋሳ ከተማ አስተዳደር ጥቅል በጀት 29 ቢሊየን 11 ሚሊየን 388 ሺህ 314 ብር፣ ለክልላዊ ፕሮግራሞች 3 ቢሊየን 600 ሚሊየን ብር፣ ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 1 ቢሊየን 206 ሚሊየን 600 ሺህ ብር እንዲሁም ለክልሉ መጠባበቂያ በጀት 200 ሚሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡

በጀቱ ከፌዴራል መንግስት ድጎማ፣ ከክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ እና  ከሌሎች የገቢ ምንጮች በሚገኘው ገንዘብ ይሸፈናል ነው የተባለው፡፡ (ኤፍቢሲ)