በመሬት አስተዳደር ዘርፍ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ስርአት እየተዘረጋ ነው

በመሬት አስተዳደር የአገልግሎት  ዘርፍ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ስርአት  እየተዘረጋ መሆኑን የሰበታ ከተማ ከንትባ ተናግረዋል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋች የመጣችውን የሰበታ ከተማ ለማሳደግና የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል የመዋቅርና የአደረጃጀት ለውጥ ለማድረግ ቅድመዝግጅት ማጠናቀቁን የሰበታ ከንቲባ አቶ ለገሰ ነገዎ አስታውቀዋል፡፡ 

የህዝቡን  ፍላጎት መሰረት ያደረገ የአገልግሎት ተደራሽነት ለማረጋገጥ በቀጣይ የሚዘረጋው አዲሱ መዋቅር አስፈላጊ መሆኑን የሰበታ የከተማ ከንቲባ  ተናግረዋል፡፡

የመሬት ይዞታዎች በ ጂ አይ ኤስ ቴክኖሎጂ በዘመናዊ የመሬት አያያዝ  የተመዘገበ ሲሆን በዚህም የተገልጋዩን   እንግልት መቀነስ እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡       

በመጨረሻም ከንቲባው  በመሬት አገልግሎት አሰጣጥ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ስርአት  መዘርጋት ትኩርት ተሠጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ የሰበታ ከተማ  መሬት አስተዳደር ለዘመናት የመልካም አስተዳደር ችግር  የነበረውን የነባር አርሶደሮች  የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ጥያቄ  እየመለሰ በመሆኑ  የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጋዮች ተናግረዋል፡፡