ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት አባላትን ሰየሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ አማካሪ ምክር ቤት አባላትን ሰይመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ባደረጉት ንግግር ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በቀን ቢያንስ 1 የአሜሪካ ዶላር በመለገስ ለተለያዩ የልማት ስራዎች ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድን የሚያማክር ምክር ቤት ማቋቋማቸውን እና ምክር ቤቱን የሚያማክሩ የምክር ቤት አባላት ዛሬ መሰየማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ አረጋግጠዋል።

በዚህም መሰረት፦

  1. ዶክተር አለምአየሁ ገብረማርያም – የምክር ቤቱ ሊቀመንበር
  2. ዶክተር ብስራት አክሊሉ
  3. አቶ ገብርኤል ንጋቱ
  4. አቶ ካሳሁን ከበደ
  5. ዶክተር ለማ ሰንበት
  6. ወይዘሮ ሉሊት እጅጉ
  7. ዶክተር መና ደምሴ
  8. ወይዘሮ ሚሚ አለማየሁ
  9. አቶ ሚኒልክ አለሙ
  10. አቶ ኦባንግ ሜቶ
  11. አቶ ሮብሰን ኢታና
  12. አቶ ታማኝ በየነ
  13. አቶ ተሽታ ቱፋ
  14. አቶ ይሄነው ዋለልኝ እና
  15. አቶ ኤሊያስ ወንድሙ የምክር ቤቱ አባላት ተደርገው ተመርጠዋል።

ከዚህ ቀደምም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ተሳትፎ ለማቀናጀትና የልገሳውን ገንዘብ ለማሰባሰብ፥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በሚል ስም ሂሳብ መከፈቱ ይታወሳል። የሂሳብ ቁጥሩም 1000255726725 ነው። (ኢዜአ)