የጣና ሐይቅ ዳርቻ ወደቦች በ400 ሚሊየን ብር ሊገነቡ መሆናቸው ተገለጸ

የጣና ሐይቅ ዳርቻ ወደቦች በ400 ሚሊየን ብር ሊገነቡ መሆናቸውን የጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ድርጅት አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙላት ፀጋ እንደገለፁት የጣና ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት አስር ወደቦች የቆዩ ከመሆናቸው የተነሳ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው ።

በዚህም ምክንያት በተጓዦች ላይ እንግልት ከመፍጠሩ በተጨማሪ ድርጅቱም ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዳያገኝ አድርጎታል ።

በመሆኑም የወደብ ግንባታው ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆንና አገልግሎቱን ቀልጣፋ ለማድረግ ከውጭ በተገኘ 400 ሚሊዮን ብር በአዲስ መልክ ለመገንባት እቅድ ተይዟል ።

ፕሮጀክቱ የሰባት ወደቦችን ደረጃ የማሳደግ እና የሁለት አዳዲስ ወደቦች ግንባታን ያካተተ ነው። የግንባታው ወጪም በኢትዮጵያና በኔዘርላንድስ መንግስት እንደሚሸፈን የአማራ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።