በኢትዮጵያ የሚከናወነው የመሠረተ ልማት ግንባታ የከተሞችን ተጠቃሚነት ያጣጣመ ሊሆን ይገባል – ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን

በኢትዮጵያ  የሚከናወነው የመሠረተ ልማት ግንባታ የከተማና የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚነት ያጣጣመ ሊሆን እንደሚገባ ምክትል  ጠቅላይ ሚንስትር  አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ሀገራዊ  የማስጀመሪያ  ዎርክሾፕ ተካሂዷል፡፡

የከተማ ልማትና  ቤቶች ሚኒስቴር የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ሀገራዊ የማስጀመሪያ ዎርክ ሾፕ አካሂዷል፡፡

አዲሱ ፕሮጀክት በአለም ባንክና በፈረንሳይ መንግስት የታገዘ ሲሆን 860 ሚሊዮን የአሜሪኮ ዶላር ተመድቦለታል፡፡

የዎርክሾፑ አላማ የከተሞችን መሠረተ ልማት በሚገባ ለመገንባት ግንባር ቀደም ተዋናይ ለሆኑት አመራሮች ግንዛቤ ለማስጨበጥ መሆኑን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል፡፡

በአዲሱ የኢትዮጵያ የከተሞች ተቋማዊና የመሠረተ ልማት መርሃ ግብር (ዩአይአይዲፒ) ቀደም ሲል የዬኤል ጂዲፒ ፕሮጀክት ተጠቃሚ በነበሩ 44 ከተሞች ቀጥተኛ ተጠቃሚ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ከተሞች በመመዘኛ እየተፈተሹ በጀት የሚለቀቅላቸው ይሆናል፡፡

በሀገሪቱ የሚከናወነው የመሠረተ ልማት ግንባታ የከተማና የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚነት ያጣጣመ ሊሆን እንደሚገባም  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል፡፡

በተለይም  የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ድህነትን ለመቀነስ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አቶ ደመቀ መኮንን አሳስበዋል፡፡

አዲሱ ፕሮጀክት ለአምስት አመታት የሚቆይ ሲሆን 117 ከተሞችን ያቅፋል፡፡ በጥቅሉ ደግሞ 7 ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡